Search This Blog

Friday, October 14, 2011

አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል??

አንዳንድ ጊዘ አለኮ......በጠራራና አድርቅ ፀሐይ በቁር የምንኮራመትበት:: አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል?? አምላክ ከትንፋሻችን ይልቅ ተጠጋግቶን በትንፋሹ እያሞቀን ግን በናፍቆቱ የምንሰቃይበት!! አንዳንድ ወቅት እኮ አለ........ጓደኞቻችን በዙሪያችን ተኮልኩለው እየወደዱን በወሪያቸው እየጠመዱን ግን በብቸኝነት የምንነፍዝበት:: አንዳን ጊዜ እኮ አለ.......አምላካችን ከ አንዳንድ ጊዜ ወደ ዘላለም ዘላለም እስኪወስደን ድረስ::

No comments:

Post a Comment