Search This Blog

Saturday, August 13, 2011

ነገረ-ሊሾ& ነገረ ህንጻ

የ አዳም ረታን " ያመጣል መንገድ ይወስዳል መንገድ"የተሰኘ ልብለድ እያነበብኩ ነው:: አዳም እዚህም  እዚያም አፈርን ያነሳሳል:: ህይወታችን ከ አፈር ጋር የተቆራኜ እንደሆነ በ ትዕምርቶች (symbols)ይጠቁማል:: "ከአፈር ነህ ወደ አፈር ትመለሳለህ" የሚለውን እውነት ያንፀባርቃል::
እውነት ነው የዕለት ከለት ኑሯችን ከ አፈር ጋር ያገናኘናል( በተለይ ከ አፈር መንገድ እና ከአፈር ቤቶች ያልተላቀቅነዎችን አፍሪካውያንን:: ብዞዎቻችን  አፍሪካውያን በመልክ እንኳን ወደ አፈር እንጠጋለን:: ስማችን እንኳን ሳይቀር አፍሪካ( አፈር ኢካ--አፈር ነህ ማለት ነው በትግረኛ) ነው:: እናም ይኼ በየቦታው ያለ አፈር አፈርነታችንን እያስታወሰን አምላካችንን እንድናስብ የህየወትን ፍጻሜን ሞትንም አንዳንዘነጋ ያደርገናል:: ግን ደግሞ ጎድቶናል:: ከንቱ እንደሚሆን ማንንነት ብቻ እንድንመላለስ አበረታቶናል:: ከ አፈር በላይ' ከሞት በላይ መሆናችንን አምነን ከፍ ብለን እንዳንኖር የአፈሩ ሽታ አደንዝዞናል::
ግን ከ አፈር የተላቀቁት ወለላቸውን ሊሾ ወይ ሴራሚክስ 'ህንፃቸውን ድንጋይ ወም ብሎኬት የሚያደርጉት ምዕራብውያንና ሌሎችስ? መጀመሪያውኑ ከ አፈር መላቀቅ ወደ ድንጋይ 'ወደ ብሎኬት 'ወደ ሴራሚክስ 'እና ወደ አስፋልት መሸጋገር ለምን ፈለጉ? ለስልጣኔ የሚለው ጥሩ የሚመስል ምክንያት ይቆዬን:: እኔ አንድ ነገር ይታየኛል:: ሞትን መፍራትቸው& እግዚአብሄርንም መናቃቸው:: ወለላቸው አፈር 'ቤታቸው አፈር 'መንገዳቸው አፈር ቢሆን ኖሮ አፈርነታቸውን በየለቱ አምላካቸውን ደግሞ ቢያንስ በየሰለስቱ ያስቡ ነበር:: ግን በሞት ፍርሃታቸው  በእግዚአብሄር ሽሽታቸው ምክንያት ወለላቸውን በሲሚንቶ ይሸፍናሉ:: ህንጻዎቻቻው በድንጋይ-ብሎኬት ይሰራሉ:: ነገሩ ተሸወዱ እንጂ ከሰማይ በታች ከ አየሩ በስተቀር አፈር ከመሆን የሚቀር ነገር የለም:: ድንጋዩም ሊሾውም የአፈር ዘር ነው:: ግን ለጊዜው ካፈር ይደበቃሉ(ላይተርፉ) ከ እግዚአብሄር ይሸሻሉ(ላያተርፉ)::
ታዲያ ይቺ አፈርን መጥላትና እግዚአብሄርን መሸሽ ወደ አፈር-ኢካም(አፈር ኢካ-አፈር ነህ)እየተዛመተች ነው:: ከአፈር ከተላቀቁ እናም አፈርነታቸውን ረስተው በትዕቢት ከታነቁ ወገኖች(ለምሳሌ ምዕራባውያን) አልተማርንም:: በርግጥ የሞት ቤት የሆነው አፈር ባሰቡት ቁጥር ልብን የሚያርድ እናም የሚያስበረግግ መሆኑ አልጠፋኝም::

ግን እውነተኛ እውነት እውነተኛም ተስፋ አለ:: ክርስቶስ እየሱስ ከ አፈር ብቻ ከመሆን አላቆ ነፍሳችንን ከሞት ነጥቆ በጉያው ሸጉጦ መንፈሳችንን በሰማያት ስፍራ ከራሱ ጋራ ሊያስቀምጥ ወዷል::ክብር ለስሙ ይሁን!!
ሐምሌ 30 '2003 ዓ.ም ረፋድ ላይ
6 ኪሎ ካምፓስ NCR  ህንጻ

No comments:

Post a Comment