Search This Blog

Thursday, June 30, 2011

ስለ ሴቶች አንገት መስበር

ስለ ሴቶች አንገት መስበር
በርግጥ አንገቷን የምትሰብር ሴት እንደ ጭዋ የምትቆጥርበት ጊዜ አልፏል:: እንዲያውም ለሴትም ይሁን ለወንድ ቀናብሎ መራመድና አንገትን ሳይሰብሩ አፍጦ ማየትና መናገር የራስ መተማመን ስሜት መገለጫ የሆኑ ይመስላል:: አሁንም ግን አንዳንድ ሴቶች አንገታቸዉን ይሰብራሉ::
ግን አሁን ሁለት አላማ ይዘው ነው:: አንድም ወጋቸውን ያልረሱ ጭዋዎች መሆናቸውን ለማሳዬት: አንድም የወንዱን ጫማ ለማዬት!!!
ስለዚህ "ሴት ልጅ የምታዬው ጫማህን ነው" የሚለውን አሉባልታ የሚያምኑበት ወንዶች ከ ሳልባጅ ተራ ከላይ የሚለበሱትንና ሱሪያቸውን በመግዛት ያለቻቸውን ጥሪት ምርጥ የተባሉ ጫማዎችን በመሸመት ያጠፋሉ::
ወደ ወንዶች እግዜር ቢፈቅድ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ:: "ቅድሚያ ለሴቶች" ብዬ ነው::
ቁም ነገር አጥታችሁበት ይሆን?
ፀጋዬ ኃ/ ስላሴ
ዘብሄረ ሃገረ ሰማያዊ

No comments:

Post a Comment