Search This Blog

Saturday, August 20, 2011

36 ብር ቅጣት!!!!???




ዛሬ ወደ መብራት ሐይል ክፍያ ጥሎኝ ሄጀ ነበር:: ስደርስ ክፍያው መፈፀም የነበረበት ከ 6-10 መሆኑን ተጨማሪም 3 ቀናት ተሰጥተው የመጨረሻ ቀን በ 13 እንደነበር እናም እንደምቀጣ ተነገረኝ:: ያሳሳተኝን ሰው ወቅቼ ለመክፈል ተዘጋጀሁ:: ዋጋውን ስጠይቅ 36 ብር ነው:: ክው እና ክውክው አልኩ:: 36 ብር የመክፈያ ቀን ስላለፈ?
የሳኣት አጠቃቀም ላይ ከባድ ችግር ያለብን እኛ አንቀጣ ማለቴ አይደለም:: ከበድ ያለ ቅጣት መጣሉም ሰው እንዝላል እንዳይሆን ያረግ ይሆናል:: ግን 36 ብር? ከመናገር ወደ ኋላ ማለት አልቻልኩም:: ፊቴን ኮስኩሼ ድምፄን ግን አለስልሼ አስከፋይዋን እንዴት 36 ብር ብዬ ጠየኩ:: "እኛ እኮ የተቀመጥነው ለመስራት ነው.......ከ 8 ቀን በላይ እንዴት መታገስ ይቻላል?" አለችኝ:: ምክንያቷ አሳማኝ እንደሆነ ነገር ግን የብሩ መጠን እጅግ ከፍ እንዳለ ተናግሪ እንደሚከተለው ፎገርኩ
"ክፍያ ያሳለፈ 36 ብር ከተቀጣ ህገ-መንግስቱን የተላለፈ እንዴት ሊቀጣ ነው?"
ሴትዮዋ ቀና ብላ ገርምማኝ "እሱን እነሱ ያውቃሉ::" አለችኝ:: እነሱ ማናቸው???
36 ብር? የህይወት ሩጫ ከ 36 ከፍሎት በድህነት እየተቆላ ለሚኖር ህዝብ 36 ብር ቅጣት?? ለምሳሌ በወር ከ 6 ብር በላይ የማይከፍሉና በዚህ ወር ሰው ታሞባቸው የሆስፒታል ቀዝቃዛና ሸታታ ወለል ላይ ተኝተው ሲያስታምሙ መድሐኒት መግዣ አጥተውም ሲቃዡ ክፍያ ያለፋቸው "እመት" ቢኖሩ 36 ብር ቢቀጡ ምን ይውጣቸዋል????
መብራት ሀይል ሆይ ቅጣቱ በየቤታችን ከሚደርሰውና ሲያሻው ከሚቆራረጠው የሀይል አቅርቦት ይልቅ አላየለም ወይ?
(በነገራችን ላይ ቅጣቱን አልከፈልኩም......በከምፒውተር ስኅተት(ምስኪኑ ከምፒውተር!!)የባለፈው ወር ሂሳብ በድጋሜ ካሁኑ ጋር ተድርቡ በመምጣቱ ምህረት ተደርጎልኛል)
//---//
ክብር ከዘላለም ቅጣት ለገላገለን ለክርስቶስ ኢየሱስ!!
ሐምሌ 14 2003 ዓ.ም
ከሳር ቤት 6 ኪሎ እስክደርስ ብሶቱ ልቤ ላይ ተሳለ::

No comments:

Post a Comment